የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ አገልግሎት
በቅርብ ቀን ይጠብቁን! የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት፣ የከተማዋን ነዋሪዎች የቆሻሻ አወጋገድ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እና ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ድርጅታችን አገልግሎቱን በይፋ ለመጀመርና ለማጠናከር እያከናወናቸው ያሉ የዝግጅት ተግባራት፡- ዓላማችን ይህ ዝግጅት ተጠናቆ አገልግሎቱ ሲጀመር፣ የከተማችን ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በቅርብ ርቀት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። “ሚዛን አማንን ንጹህ፣ ውብ እና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራን ነው!” ማሳሰቢያ፦ አገልግሎቱ የሚጀመርበትን ትክክለኛ ቀን እና ዝርዝር መረጃዎችን በቅርቡ በድረ-ገጻችን እና በማስታወቂያ ሰሌዳዎቻችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።


